የአማራ ብዙሔራዊ ክልላዊ መንግስት ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ

መግቢያ

የክልሉ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ በ1985 የተቋቋመ ሲሆን እስከ 1987 ዓ/ም ድረስ በቢሮ ደረጃ ማስታወቂያ ቢሮ ተብሎ ተዋቅሮ እንቅስቃሴ ሲያድእርግ ቆይቷል። አደረጃጀቱም የሬዲዮና ቴሌቪዥን የፕረስ ህዝብ ግንኙነተ እንድሁም የዜና አገልግሎት መመሪያዎች ነበሩት። በዚህ ወቅት በየዘርፉ የሚሰሩ ዘገባዎች ለማዕከል ሚዲያዎች ለኢትዮጵያ ሬዲዮ ቴሌቪዥንና ጋዜጦች በመላክ ነበር ለስርጭት የሚበቁት።

 

በ1988 በአዋጅ ቁጥር 4/1988 መሰረት ከባህልና ቱሪዝም ቢሮ። በዚህ ወቅት ቀደም ብሎ በ3 መምሪያዎች ስር የነበረዉየሚዲያ ዘርፍ በአንድ መመሪያ ስር ተጠቃለለ። ማስታወቂያ መምሪያ በመሆን በስሩም የሬዲዮ፤ የቴሌቪዥን፤ የዜና አገልግሎት እና የፕረስ ዋና ክፍሎች ተዋቅረው ስራውን በተመሳሳይ መልኩ ሲያከናውኑ ቆይቷል።

የመገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 56/1993 ዓ/ም በድጋሜ የተደራጀ ሲሆን በዚህ አዋጅ መሰረት ተጠሪነትም ለክልሉ መንግስት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሆኗል። አዋጅ ቁጥር 88/1995 የኤጀንሲውን ተጠሪነት ለአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት በማድረግ ተቋሙን በድጋሜ አደራጅቷል። ኤጀንሲው የሚተዳደረው በአዋጅ ቁጥር 120/1998  የብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ የሚል ስያሜ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ የተቋሙ መለያ በዙሃነ መገናኛ ድርጅት የሚል ነበር። በአዋጅ ቁጥር 88/1995 መሰረት ኤጀንሲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት አሉት፤

       1. ለክልሉ ህዝብ ጠቀሜታ ያላቸውን አስፈላጊ ዜናና ዜና ነክ መረጃዎችን በፕረስ ውጤቶች፣በሬዲዮና ብቴሌቪዥን ማሠራጫዎች  ለህዝብ ያስተላልፋል፤ ለዚህም እንዲረዳው እንደ አስፈላጊነቱ መደበኛ የጋዜጣ፣ የመጽሄትና ሌሎች ህትመቶች እንዲሁም የሬዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እንዲኖሩት ያደርጋል፣

     2.የመንግስትን ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች፣ ፖሊሲዎችና ህጎች ልህዝብ ያስተዋዉቃል፤ ህዝቡም ብስትራቴጂዎቹ፣ ብፖሊሲዎቹና፣ በህጎቹ ላይ ሐሳቡን እንዲልዋወጥባቸዉ፣ እንዲመክርባቸው አስተያየቱን እንዲሰጥባቸው ብዚህም ብሔራዊ መግባባት ላይ እንዲደርስ ምቹ የሚዲያ መድረኮችን ይፈጥራል፣

     3. የክልሉ ነዋሪ ህዝብ ስለሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ያለዉን ግንዛቤ ልማጎልበት የሚረዱ ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን ክትሞክሮዎች ጋር እያዛመደ ያቀርባል፣

     4. ነፃ የህዝብ አስተያየቶችንና ጥቆማዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል፣ የሚመለከታቸውንም አካላት በመጠየቅ ያጣራል፣ ውጤቱንም መልሶ ለህዝብ የገልፃል፣

   5. የህዝቡን ጠቅላላ እውቀት የሚያዳብሩና የመዝናናት ፍላጐቱን የሚያረኩ ልዩ ልዩ ጽሁፎችንና የሬዲዮም ሆነ የቴሌቪዥን ዝግጅቶችን እየሠራ በተለያዩ ዘዴዎች ያሠራጫል፤

     6.ወቅታዊነት ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ተከታትሎ ይዘግባል፣

  7. የፎቶግራፍና የተንቀሳቃሽ ምስል ዶክመንቴሽን፣ የህትመትና የማስተዋወቂያ /Advertising/ አገልግሎቶችን ይሠጣል፣

  8.ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ የህትመት አገልግሎቶችን፣ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ኘሮግራሞች ማቀናበሪያና ማሰራጫዎችን፣ የዜናና መረጃ ማስተላለፊያ ወይም ማሸጋገሪያዎችን እንዲሁም ለተመሳሳይ አገልግሎቶች የሚውሉ ሌሎች ተቋማትን እና መሣሪያዎችን በተገቢው ሥፍራ ይተክላል፣ ያቋቁማል፣ ያደራጃል፣ ያስተዳድራል፣

  9. ለሚሠጠው አገልግሎት ተመጣጣኝ ዋጋ ያስከፍላል፤ እንደአስፈላጊነቱም በከፊልም ሆነ በሙሉ ከክፍያ ነፃ አገልግሎት ሊሠጥ ይችላል፤

  10. በአገሪቱ ህግ መሠረት በአገር ውስጥና በውጪ አገር ካሉ ተመሣሣይ ድርጅቶች ጋር ዜናዎችንና መረጃዎችን ለመለዋወጥም ሆነ የሥልጠና እና የልምድ ልውውጦችን ለማድረግ የሚያስችሉትን የሥራ ግንኙነቶች ይመሠርታል፣

 11. በአገር ውስጥና በውጭ አገር ከሚገኙና የኤጀንሲውን ቴክኒካዊ አቅም ለማጎልበት ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኝነቱ ካላቸው ድርጅቶች ጋር በክልሉና በአገሪቱ ፖሊሲዎችና ህጐች መሠረት አብሮ ይሰራል፣

 12. የክልሉ ብዙሐን መገናኛዎች ስለሚስፋፉበትና በተስማሚ ቴክኖሎጂ ስለሚደራጁበት ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ስለሚሰጥበት ሁኔታ በማጥናት ሐሳብ ያቀርባል፤ ሲፈቀድም በስራ ላይ ያውላል፤

 13. የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በስሙ ይከሣል፣ ይከሰሳል፣

 14. ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ሌሎች ህጋውያን ተግባራትን ያከናውናል፡፡

 

የአማራ B/@‰êE ክል§êE mNGST ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ :Y "የአማራ ክልል ሚዲያዎች በክልሉ ብሎም mላው አገሪቱ ህዝብ ዘንድ ከሌሎች ሚዲያዎች በላቀ ተአማኒነትና ተመራጭነት ያላቸው የመረጃ ምንô ሆነው ማየት"s!çN tL:÷WM "ብቃት ያለው የሚዲያ አሰራርን በማስፈን በክልሉ የሚከናወኑ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን በመዘገብና ህዝቡ ሀሳቡን በነፃ የሚያንሸራሽርባቸውን መድረኮች በመፍጠር ብሔራዊ መግባባትን ማጋገጥና ለክልሉ ልማት መፋጠን ገንቢ ሚና መጫወት" ነው፡፡

 

 

 

 የኤጀንሲው ድርጅታዊ መዋቅር       የብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ሠራተኞች ሲቪ   

        

Latest Bekur Publication 
  • Yekatite 29, 2002

  • B E K U R
  • Yekatite 22, 2002

  • B E K U R
    12345678910...
    Latest Radio Programs 
  • Tuesday TV Program
  • Download and view the entire media here
  • Tekemit 16,2002 - ZENA
  • Download and view the entire media here
    12345678910...
    Latest FM Radio Programs 
  • Tekemit 16,2002 - YEFEKER TEMOKERO

  • Download and view the entire media here
  • Tekemit 16,2002 - KINE TIBEB

  • Download and view the entire media here
    12345678910...
    Latest TV Programs 
  • Tuesday TV Program

  • Download and view the entire video here
  • sunday TV program

  • Download and view the entire video here
    12345678
    Advertisement 
    Search AMMA Website

     

    Newsletter
    Register to the site for free, and subscribe to the newsletter. Every month you will receive new articles and special content not available elsewhere on the site, right into your e-mail box!

    Archived Newsletters