:

የሰንደቅ ዓላማ ቀን መከበሩ በሀገሪቱ የተፈጠረውን ብሄራዊ መግባባት ይበልጥ እንደሚያጠናከረው የአማራ ክልል የሴቶችና የወጣቶች ማህበራት አስታወቁ።

 

የክልሉ ሴቶች ማህበር ዋና ጸሐፊ ወይዘሮ ማሪቱ ፈንታሁን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የሰንደቅ ዓላማ ቀን መከበር በሀገሪቱ የተገነባ ያለውን የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲ ስርዓት ለማጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።

 

በዓሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ መከበሩ ለሰላም፣ ለልማትና ለዲሞክራሲ የቆመውን የሰንደቅ ዓላማ መርህ ለመዘከርና ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ የላቀ ፋይዳ እንዳለው ዋና ጸሐፊዋ ተናግረዋል።

 

በመከባበር ላይ የተመሰረተውን የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነትና ብሄራዊ መግባባት ለማጠናከር እንደሚረዳም አመልክተዋል።

 

በተለይ ጾታዊ መብታቸው እንዲከበር ህገ-መንግስታዊ ዋስትና ላገኙት ሴቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ልዩ ትርጉም አለው ያሉት ወይዘሮ ማሪቱ፣ የማህበሩ አባላት ዕለቱን በልዩ ድምቀት እንደሚያከብሩት አስታውቀዋል።

 

የአማራ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር ወጣት መንግስቱ በላይ በበኩሉ የሰንደቅ ዓላማ ቀን መከበር የሀገሪቱን መልካም ገጽታ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍና የሀገር ፍቅር ስሜትን ለወጣቱ ትውልድ ለማውረስ እንደሚስችል ገልጿል።

 

የሰንደቅ ዓላማ ቀን ወጣቱ ትውልድ በአዲሱ ሚሌኒየም ድህነት ለማስወገድ ተግቶ እንዲሰራ ከፍተኛ የመነሳሳትና የሀገር ፍቅር ስሜት የሚፈጥር መሆኑንም ወጣት መንግስቱ ገልጿል።

(source: ENA)


How would you rate this article?

User Feedback

 

Post your comment
Name:
E-mail:
Comment:
Insert Cancel

Latest Bekur Publication 
  • Pagumie 1, 2002

  • B E K U R
  • Nehasie 24, 2002

  • B E K U R
    12345678910...
    Latest Radio Programs 
  • NEHASIE 06,2002 - KETARIK MAHDER
  • Download and view the entire media here
  • NEHASIE 06,2002 - LIMAT
  • Download and view the entire media here
    12345678910...
    Latest FM Radio Programs 
  • NEHASIE 05,2002 - Ethiopia

  • Download and view the entire media here
  • NEHASIE 04,2002 - ketark Mahder

  • Download and view the entire media here
    12345678910...
    Latest TV Programs 
  • Friday 14-12-02

  • Download and view the entire video here
  • wednesday 12-12-02

  • Download and view the entire video here
    12345678910...
    Advertisement 
    Search AMMA Website

     

    Newsletter
    Register to the site for free, and subscribe to the newsletter. Every month you will receive new articles and special content not available elsewhere on the site, right into your e-mail box!

    Archived Newsletters